«የሜርክል ዘመን አላበቃም »

አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:10 ደቂቃ
08.12.2018

ሜርክልን የተኩት አነግሬት ክራምፕ ካረንባወር

የጀርመን ክርስቲያን ዴሞክራት ፓርቲ በጀርመንኛ ምህጻሩ ሴዱኡ ሀምበርግ ላይ ትናንት ስብሰባውን ሲያካሂድ ላለፉት 18 ዓመታት ፓርቲውን በሊቀመንበርነት የመሩት የሀገሪቱ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክልን የሚተካ ሊቀመንበር መርጧል።

ሜርክልን እንዲተኩ በአብላጫ ድምፅ የተመረጡት የ56 ዓመትዋን አነግሬት ክራምፕ ካረንባወር ቀደም ብለው ፓርቲውን በፀሐፊነት ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን የሜርክል ቀኝ እጅ መሆናቸው ይነገራል። ለዚህም ይመስላል ሜርክል በሊቀመንበርነትም በመራሂተ መንግሥትነትም መቀጠሉ በቃኝ ብለው ተራውን ለሌሎቹ የፓርቲው አባላት ቢለቁም የክራምፕ ካረንባወር መመረጥ ያው እሳቸው እንዳሉ ያህል ነው የሚል አስተያየት ከፖለቲከኞች እና ከጋዜጠኞች ያስከተለው። የDW ጀርመንኛው ክፍል ባልደረባ የሆነችው ኢንስ ፖል ሜርክል በመራሂተ መንግሥትነት ይቆያሉ ስትል የጻፈውን አስተያየት እና ሃተታ የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል እንደሚከተለው ተርጉሞታል።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል/ኢንስ ፖል

ሸዋዬ ለገሠ

ተዛማጅ ዘገባዎች

ተከታተሉን