ኢትዮጵያ

አፍሪቃ

ዓለም፣ አውሮጳ/ጀርመን

ኤኮኖሚ

ሳይንስ እና ህብረተሰብ፣ ጤና እና አካባቢ

ስፖርት

ባህል

ወጣቶች

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት

ዝግጅቶቻችን በድምፅ

የዕለቱን ዝግጅት ለማዳመጥ 16:00 - 17:00

የአንድ ሣምንቱ የስርጭት ኮሮጆም "ዝግጅት"ን በመጫን ሊገኝ ይችላል። የአማርኛ፣ የኪስዋሂሊ፣ የሀውሳ፣የእንግሊዝኛ፣ የፈረንሣይኛ እና የፖርቱጊዝኛ ቋንቋ ሥርጭት በሚተላለፍበት ጊዜ በኢንተርኔት በInternet Explorer 8 በቀጥታ ማድመጥም ይቻላል። በፌስቡክ፣ በዋትስአፕ እና በviber public chat DW Amharicም ልታገኙን ትችላላችሁ። አስተያየታችሁ ዓቢይ ግምት የሚሰጠው ነው፤ በ +49-228-429-164995 ደውሉልን። በዕለቱ ዓቢይ ርዕስ ላይ በ+49 -162-1056831 በSMS አስተያየት ላኩልን። ባጠቃላይ በዝግጅታችን ላይ አስተያየታችሁን በኢሜይልም ልትልኩልን ትችላላችሁ።

amharic@dw.com

ተፅኖ ፈጣሪ አፍሪቃዉያን ሴቶች

ከፍተኛ ድል ለኢትዮጵያ ሴቶች

አምባሳደር ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ከጥቅምት 15 ቀን፤ 2011 ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር ሆዉ ተሾመዋል፡፡ አምባሳደር ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዚደንት ናቸዉ። የወንዶች የፖለቲካ እና ኤኮኖሚ የበላይነት በሚታይበት ኢትዮጵያ አምባሳደር ሳህለ ወርቅ ወደ ርእሰ ብሔርነት ሥልጣን መምጣት ለሃገሪቱ ለሴቶች ከፍተኛ ድል ሆኖ ታይቶአል። ከርዕሰ ብሔር አምባሳደር ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ሌላ የሃገሪቱ የመከላከያ ሚኒስቴርነት ሥልጣንነትን ጨምሮ አዲሱ ካቢኔ ገሚሱ ሴቶች ከፍተኛ ባለስልጣናት ሆነዋል።

ተፅኖ ፈጣሪ አፍሪቃዉያን ሴቶች

በአፍሪቃ የመጀመርያዋ ተመራጭ ሴት ፕሬዚዳንት

ኤልን ጆንሰን ሴርሊፍ በዴሞክራስያዊ ምርጫ ወደ ስልጣን የመጡ የመጀመርያዋ አፍሪቃዊት ፕሬዚዳንት ናቸዉ። ሴርሊፍ ከጎርጎረሳዉያኑ 2006 እስከ 2018 ዓ.ም የላቤርያ ፕሬዚዳንት ሳሉ ሥራ አጥነትን፤ ሃገራቸዉ ያለባትን እዳ ለመቅረፍና በሴራሌዮን የኤቦላ ቫይረስ እንዳይሰራጭ ተግተዉ ሰርተዋል። ለሴቶች ደሕንነትና ፍትህ ላበረከቱት አስተዋጽኦ በጎርጎረሳዊዉ 2011 የሰላም ኖቤል ተሸላሚም ሆነዋል። ሰርሊፍ ዛሬ በተመድ የአህጉሪቱ የፍልሰት ጉዳይ ተመልካች ቢሮ ሊቀመንበር ናቸዉ።

ተፅኖ ፈጣሪ አፍሪቃዉያን ሴቶች

ሩዋንዳዊቷ ከፍተኛ ጠበቃ

ሩዋንዳ ከ10 ዓመት ወዲህ ከፈረንሳይኛ ይልቅ ኢንጊሊዘኛ የሥራ ቋንቋ እንዲሆን ቢደነገግም የሩዋንዳ የቀድሞ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዊዝ ሙሲኪዉቦ በጎርጎረሳዊዉ 2019 የሩዋንዳ የፈረንሳይኛ ቋንቋ ማኅበረሰብ ዓለምአቀፍ ድርጅት ተጠሪ እንዲሆኑ ተሾመዋል። የሉዊዝ መመረጥ በተለይ በዲፕሎማሲዉ ሥራ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠዉ ነዉ ተብሎአል። ሉዊዝ ሙሲኪዉቦ ከፈረንሳዩ ፕሬዚደንትና ከሌሎች የዉጭ ሃገራት ባለሥልጣናት ድጋፍን አግኝተዋል።

ተፅኖ ፈጣሪ አፍሪቃዉያን ሴቶች

አንዲት ሴት እና 193 ሃገራት

ከጎርጎረሳዉያኑ 2017 ጀምሮ በተመድ ተለዋጭ ፀሐፊ ሆነዉ በማገልገል ላይ ያሉት ናይጀርያዊትዋ አሚና ሞሐመድ ሌላዋ የአህጉሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣን ናቸዉ። አሚና ሞሐመድ ከጎርጎረሳዊዉ 2002 እስከ 2005 ድረስ በተመ በአምዕቱ የልማት ግቦች ዘርፍ አገልግለዋል። ከዝያ በመለጠቅ የቀድሞዉ የተመድ ዋና ፀሐፊ የባን ኪሙን ልዩ አማካሪም ነበሩ። በተመድ የአማካሪነት ሥራ ተልኮአቸዉን ሲያጠናቅቁ ደግሞ፤ በናይጀርያዉ ፕሬዚደንት ሙሃማዱ ቡሃሪ የሥልጣን ዘመን የሃገሪቱ የአካባቢ ተፈጥሮ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነዉ አገልግለዋል።

ተፅኖ ፈጣሪ አፍሪቃዉያን ሴቶች

እዳን ለማቃለል የታገሉት ናሚቢያዊት

ናሚቢያዊቷ ሳራ ኩጎንጌላዋ አማዲላ ከጎርገረሳዉያኑ 2015 ጀምሮ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዉ ናሚቢያን እያስተዳደሩ ነዉ። አሚና በሃገሪቱ የተመረጡ የመጀመርያዋ የሴት ጠቅላይ ሚኒስትርም ናቸዉ። ጠቅላይ ሚኒስትር አሚና ወደዚህ ስልጣን ከመምጣታቸዉ በፊት የሃገሪቱ የገንዘብ አስተዳደር ሚኒስትር ሆነዉ አገልግለዋል። በዚህ ስልጣናቸዉ ሃገሪቱን ከእዳ ሊያቃልል የሚችል መርህ ቀርፀዉ ናሚቢያ ከተሸከመችዉ እዳ አቃለዋታል። የኤኮኖሚ ጉዳይ ምሁርዋ ናሚቢያዊት ከጎርጎረሳዉያኑ 1995 ጀምሮ የናሚቢያ ብሔራዊ ምክር ቤት አባልም ናቸዉ።

ተፅኖ ፈጣሪ አፍሪቃዉያን ሴቶች

በሃገራቸዉ የነዳጅ ዘይት የነገሡት ባለኃብት

ኢዛቤል ዶሻንቶስ በአንጎላ አወዛጋቢ ባለሥልጣን ናቸዉ። ከጎርጎረሳዉያኑ 2016 ጀምሮ የአንጎላ የነዳጅ ምርት ኩባንያን በዳይሬክተርነት የመሩት ኢዛቤል፤ የቀድሞ ፕሬዚደንት ዶሻንቶስ ልጅ ናቸዉ። አሁን ወደ ሥልጣን የመጡት የአንጎላ ፕሬዚዳንት ለባለሥልጣናት በዝምድና የሚሰጥን ድጋፍም ሆነ ሥራ የሚቃወሙ በመሆናቸዉ ወደ ስልጣን እንደመጡ ነበር የቀድሞዉ ፕሬዚደንት የኤድዋርዶ ዶሻንቶስን ልጅ ኢዛቤልን ከነበራቸዉ ስልጣን ያነስዋቸዉ። ሆኖም ግን ኢዛቤል ዶሻንቶስ ሲያስተዳድሩት የነበረዉን የሃገሪቱን የነዳጅ ዘይት ኩባንያ ገቢ ዱባይ ወደሚገኝዉ የግል ባንካቸዉ ያከማቹ«ይሰርቁ»ስለነበር አሁንም በሃብት ዳጎስ እንዳሉ ናቸዉ።

ተፅኖ ፈጣሪ አፍሪቃዉያን ሴቶች

ያልተነገረላቸዉ ተፅኖ ፈጣሪ የኮንጎ ሴት

ምስጢር በመጠበቅና ከፍተኛ ጥንቃቄያቸዉ የሚታወቁት ጃኔት ካቢላ የዴሞክራቲክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት የጆሴፍ ካቢላ መንትያ እህት ናቸዉ። ጃኔትና ጆሴፍ ደግሞ የቀድሞዉ የኮንጎ ፕሬዚዳንት ልጆች መሆናቸዉ ነዉ። ጃኔት ካቢላ በዴሞክራቲክ ኮንሆ የፓርላማ አባል ናቸዉ። ከዝያ በተጨማሪ የአንድ የቴሌቭዥን፤ ራድዮና የኢንተርኔት ማሳረጫ ኩባንያ ባለቤት እና አስተዳዳሪ ናቸዉ። ጃኔት አንድ ወቅት ለአንድ የፈረንሳይ መጽሔት በሰጡት ቃለ ምልልስ በሃገራቸዉ ከሚገኙት ተፅኖ ፈጣሪ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል አንዷ ነኝ ብለዉ መናገራቸዉ ይጠቀሳል።

ተፅኖ ፈጣሪ አፍሪቃዉያን ሴቶች

ወጣትዋ የማሊ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር

ወጣትዋ የማሊ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካሚሳ ካማራ በሃገሪቱ ታሪክ የተመረጡ የመጀመርያዋ ሴት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናቸዉ። የ 35 ዓመትዋ ወጣት ሚኒስትር ለዳግመኛ የሥልጣን ዘመን ለተመረጡት ለማሊዉ ፕሬዚዳንት ባቡከር ኪየታ ካቢኔ ከተሾሙት 11 ሴት ሚኒስትሮች መካከል አንዷ ናቸዉ። የማሊ የመንግሥት የሚንስትሮች ምክር ቤት በአጠቃላይ 32 ሚኒስትሮችን ያቀፈ ነዉ።

ተፅኖ ፈጣሪ አፍሪቃዉያን ሴቶች

ናይጀርያዊቷ ባለሐብትና በጎ አድራጊ

ናይጀርያዊቷ ቱጃር ፍሎሩንሾ አላካጃ የ 1,6 ቢሊዮን ዶላር ባለንብረት መሆናቸዉ ይነገርላቸዋል። የነዳጅ ጥሪ ሃብትን በታደለችዉ ናይጀርያ ፍሎሩንሾ አላካጃ «ፋማ ኦይል» የተባለ የነዳጅ ማምረቻ ኮባንያ አስተዳዳሪና ባለንብረት ናቸዉ። ይኸዉ ንብረታቸዉ ታድያ በሃገሪቱ ከሚኖሩ ዜጎች በሐብት ክምችት ሦስተኛዋ የናይጀርያ ቱጃር አድርጎአቸዋል። እንደ አንጎላዋ ኢዛቤል ዶሻንቶስ ሁሉ ናይጀሪያዊቷ ፍሎሩንሾ አላካጃም በዓለማችን ከሚገኙ በጣም ቱጃሮች ከሚባሉት ጥቂት ሰዎች መካከል አንድዋ ናቸዉ። የ 67 ዓመትዋ ናይጀርያዊት ባለሐብት በአቋቋሙት የሕጻናት መርጃ ተቋም ወላጆች የሌላቸዉን ልጆች ይረዳሉ።

ዜና በእንግሊዝኛ

ዶይቸ ቬለ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች

አስተያየትዎ
አስተያየትዎን ለመላክ የአስተያየት መስጫውን ፎርም ይጠቀሙ።
የጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የጀርመን ጉብኝት

ትዉዉቅና መስተንግዶ

ዶክተር ዐብይ ወደ ቡድን 20 ጉባኤ ከመግባታቸው በፊት ባልተጠበቀ ሁኔታ በርሊን ሊቀበሏቸው የወጡ ኢትዮጵያውያን ወደተሰሰቡበት ስፍራ ሄደው በመጨበጥ እና በማቀፍ እንዲሁም እጃቸውን በማውለብለብ ሰላምታቸውን አቅርበዋል። በዶክተር ዐብይ ያልተጠበቀ ሰላምታ የተደሰቱ እና የተገረሙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ምስጋናቸውን አቅርበውላቸዋል። መልካም ምኞታቸውንም ገልጸውላቸዋል።

የጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የጀርመን ጉብኝት

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተስፋን የሰነቁት ታዳጊ ሕጻናት

ዶክተር ዐብይ በርሊን የመጡት ከባዱ ክረምት በተቃረበበት ወቅት ላይ እንደመሆኑ ሊቀበላቸው የመጣው ኢትዮጵያዊ አለባበሱን ከወቅቱ ብርድ ጋር አስተካክሎ ነበር የወጣው። ከዚሁ ጋር የኢትዮጵያን ባንዲራ ያነገበ እና የለበሰው ቁጥር ቀላል የሚባል አልነበረም። ሕጻናትም እንደ ወላጆቻቸው በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አምረው ደምቀው ነበር ሊቀበሏቸው የመጡት።

የጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የጀርመን ጉብኝት

አንድነት በበርሊኑ አደባባይ

የኦነግን አርማ እና የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ የያዙ ኢትዮጵያውያን በበርሊኑ የብራንድንበርግ ቶር አደባባይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን ሲጠባበቁ።

የጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የጀርመን ጉብኝት

ታዳሚዎች በሃገሪኛ ሙዚቃ ሲዝናኑ

የፍራንክፉርት «ኮሜርስ ባንክ አሬና»ታዳሚዎች የጠ/ሚ ዐብይ አሕመድን መምጣት በመጠባበቅ ባንዲራቸዉን እያዉለበለቡ በሃገሪኛ ሙዚቃ ሲዝናኑ ነበር።

የጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የጀርመን ጉብኝት

ጥያቄም አለን

በፍራንክፈርት ኮሜርስ ባንክ አሬና የታደሙ ኢትጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይን መምጣት ሲጠባበቁ

የጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የጀርመን ጉብኝት

የአባቶቻችን ፀሎት

ስብሰባው በሃይማኖት አባቶች ፀሎት እና በሽማግሌዎች ምርቃት ነው የተጀመረው። እነርሱም በአውሮጳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ፣ ፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያን እና የእስልምና እምነት መሪዎች እንዲሁም አባ ገዳ ናቸው።

የጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የጀርመን ጉብኝት

ሀገሬ አንቀላፍታ ይሆናል እንጂ አልሞተችም

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በጀርመንኛ ቋንቋ ሰላምታ በማቅረብ በጀመሩት ንግግር "አሁን ያላየነውን የምናይበት፤ ያልሞከርነውን የምንሞክርበት ጊዜ ነው" ብለዋል ። "ኢትዮጵያ ማንም ተነስቶ በወደደው ልክ እና ፍላጎት እንደ ቂጣ የሚጠፈጥፋት ሳትሆን ታላቅ ህዝብ የመሰረታት ታላቅ ሀገር»መሆንዋንም ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በታዳሚው ጥያቄ ይህን አባባላቸውን ደግመውታል። "ሀገሬ አንቀላፍታ ይሆናል እንጂ አልሞተችም" ብለው ሲናገሩም በከፍተኛ ድምፅ የታጀበ ድጋፍ ተቸሯቸዋል። በአዉሮጳ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ከዉጭ ሆኖ ከመተቸት ባሻገር በኢኮኖሚዉም ሆነ በፖለቲካዉ እንዲሳተፉም ጋብዘዋል።

የጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የጀርመን ጉብኝት

ጠቅላይ ሚንስትሩን የማየት ጉጉት

«አንድ ሆነን እንነሳ፣ ነገንም እንገንባ» የተሰኘው የፍራንክፈርቱ መርህ ግብሩ ከሰዓት በኋላ እንደሚጀመር ቢታወቅም ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በኮሜርስ ባንኩ አሬና ስታድዮም መታደም የጀመሩት ገና ከጠዋቱ ነበር ።

የጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የጀርመን ጉብኝት

ዉቡ ባህላችን

በኢትዮጵያ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች አልባሳት የተዋቡ እንስቶች በፍራንክፈርቱ «ኮሜርስ ባንክ አሬና ስታድዮም » ባህላዊ ትዕይንቶች ሲያቀርቡ።

የጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የጀርመን ጉብኝት

የአፋር ባህላዊ አለባበስ

ከፍራንክፈርቱ ኮሜርስ አሬና ስታድዮም ታዳሚዎች መካከል እነኚህ በአፋር ባህላዊ አለባበስ እና ጌጣጌጥ የደመቁ ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል።

የጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የጀርመን ጉብኝት

አንድ ሆነን እንነሳ ነገነም እንገንባ

«አንድ ሆነን እንነሳ ነገነም እንገንባ» የፍራንክፈርቱ የዶክተር ዐብይ እና አውሮጳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስብሰባ ዓላማ ነው። ዶክተር ዐብይ በስብሰባው ላይ ባሰሙት ንግግር «አሁን እጃችን ላይ ያሉት ሁለት ነገሮች ናቸው ነፃነት እና ተስፋ፤ እነዚህን ሁለቱን ይዘን በትብብር እና በአንድነት ከሰራን የምንሻት ኢትዮጵያን ከመፍጠር የሚያግደን ኃይል አይኖርም» ብለዋል።

Albanian Shqip

Amharic አማርኛ

Arabic العربية

Bengali বাংলা

Bosnian B/H/S

Bulgarian Български

Chinese (Simplified) 简

Chinese (Traditional) 繁

Croatian Hrvatski

Dari دری

English English

French Français

German Deutsch

Greek Ελληνικά

Hausa Hausa

Hindi हिन्दी

Indonesian Indonesia

Kiswahili Kiswahili

Macedonian Македонски

Pashto پښتو

Persian فارسی

Polish Polski

Portuguese Português para África

Portuguese Português do Brasil

Romanian Română

Russian Русский

Serbian Српски/Srpski

Spanish Español

Turkish Türkçe

Ukrainian Українська

Urdu اردو